ጊዜው
ትንሽ ቆየት ብሏል፡፡ ለበርካታ ጊዜ አዲስ አበባ ሲመላለስ የማውቀው አያቴ እርጅና ተጭኖት ብቅ አልል ስላለ በዛውም ገጠሩን ማየት
ስላማረኝ ሁለቱንም ልሳለማቸው ብዬ ጉዞ ጀመርኩ፡፡ ከዚህ ቀን አስቀድሞ ነፍስ ካወቅሁ በኃላ ማለቴ ነው እንዲህ ያለ ገጠር ውስጥ
ገብቼ አላውቅም፡፡ በዛ ወቅት የመንግስት መገናኛ ብዙሀን እስከዛሬ የሐገሪቱን የጥቅም እፍታ ለብቻው ሲያግበሰብስ የነበረው ክልል
ይህ እንደነበር ስለሚያወሩ የነበረኝ ምናባዊ ስዕል ትልቅ ነበር፡፡
አባይን
ከተሸገርኩ በኋላ የማየው ትዕይን ግራ አጋባኝ፡፡ ያደፈ ጥብቆ ያደረጉ፣ ደሳሳ ጎጆዎቻቸው አካባቢ የከሱ የገረጡ ህጻናት እና ከብቶች
የሞሉባቸው ጉስቁልናቸው እስከዛሬ ካየኋቸው ኢትዮጵያውያን የከፋ ህዝቦች ነበር የሚታዩኝ፡፡ የቆርቆሮ ቤት መኖር ለአካባቢው እንደስልጣኔ
ተቆጥሮ ባለቆርቆሮ ቤቱ መንደር ይባላል ፡፡ በጉዞዬ ውስጥ በየማኃሉ የማገኛቸው ከተሞችን “ከተማ” ያልኳቸው ሌሎች ስላሏቸው
ብቻ ነው፡፡ በዛ ላይ አንዱ ከአንዱ ያለው ርቀት ያስደነግጣል፡፡ በትንሹ ከአዲስ አበባ 200 ኪ.ሜ በማይሞላው ርቀት ላይ የምትገኘው
አዋሳ እስክንደርስ ድረስ ስንት ትንንሽ ከተሞችን እንደምናይ ሳስበው ይህ ክልል አሳዘነኝ፡፡ 'ገጠሬነትን ክብር አድርጎ ራሱን ሲበላ
የኖረ መሆኑን የሚነግረው አጥቷል ማለት ነው' ስል አሰብኩ፡፡ ባህርዳር ስደርስ ተስፋ ቆረጥኩ . . . ብዙም የሚጋነንልላት አልሆነችልኝም፡፡
ያኔ በነበረው ህግ መሰረት አንድ የህዝብ ትራንስፖርት ወዲህ ሲመጣ ማደሪያውን የሚያደርገው የግድ ባህርዳር ላይ ነበር፤ ከመሸ መጓዝ
አይፈቀድም፡፡
ከመኪና
እንደወረድን ዳግመኛ ደብረታቦር የሚሄድ ሎንቺና ፈላልገን አገኘንና ከመሸ ገባን፡፡ በስም እና በዘፈን ብቻ አውቃቸው የነበሩትን
አሞራ ገደል፣ ደንቢያ፣ ወረታን “በዚህ ነው” “ይሄ ነው” ባሉኝ ቁጥር እየተደነቅኩ እና እየተሸማቀቅኩ ነበር አጓጓዜ፡፡ ያኔ ነው
“ለአፍ ዳገት የለውም” ብሂል የገባኝ፡፡ አሁን እነዚህ የደቀቁ እና የፈራረሱ ከተሞች ናቸው ለዘፈን በቅተው ድፍን አዲስ አበቤን
ሲያምሱት የከረሙት? አልኩኝ ለራሴ፡፡ (በወቅቱ በርካታ የባህልና
ዘመናዊ ሙዚቀኞች ጎጃምን እና ጎንደርን እየጠቀሱ ከከተማም አልፈው ጎጥና መንደሩን፣ ሳርና ቅጠሉን እያነሱ እንዲዘፍኑ የተገደዱ
ይመስሉ ነበር)
እንደውም ሳስበው ምናልባትም ለክልሉ እንዲህ ጠላት ያበዙበት ዘፈኖቹ ይመስሉኛል፡፡ ያልተመቸውን
የሌለውን እያቆለጳጰሱ የዘረፈ አስመስለው ያቀረቡት ለማለት ከጅያለሁ፡፡
ደብረታቦር፡-
አስገራሚ ነው! ከአንድ መቶ ሃምሳ አመታት በፊት በከተማነት የምትታወቅ ቢሆንም ዛሬ መንደርነት ትልቅ ክብር አለው፡፡ ድንጋጤዬ
እየገዘፈ ነበር የሔደው፡፡ ሁለት ቀን ከገጠር ዘመዶች በቅሎ ይዘው እንዲመጡ መልዕክት ለመስደድ በገበያ ውስጥ ሰው ስናፈላልግ ቆየን.
. . .፡፡ ሰው አግኝተን መልክታችንን ከነገርን በኋላ ግማሹን መንገድ ለማጋመስ ቀድመን ተነሳን፡፡ ካረፍንበት ሆቴል ልንወጣ ስናኮበኩብ
አብረውኝ ከአዲስ አበባ የመጡት ሐገሩን ጠንቅቀው የሚያውቁት ወዳጆቼ የምንነግርህ ነገር አለ ብለው በስርአት እንዳዳምጣቸው ጠየቁኝ፡፡
“የሔውልህ
ከዚህ በኋላ በምንም አይነት ማንም ሰው ስምህን ቢጠይቅህ እከሌ ነኝ አትበል፡፡ የማን ዘመድ ነህም ብትባል አትናገር” አሉኝ፡፡
ግራ
ተጋባሁ. . . “ለምን?”
“ነገርንህ
በቃ! ሲያነጋግሩህ እኛ መልስ እንሰጣለን፤ አንተ ቀድመህ መልስ አትስጥ ብቻ”
ምን
እየተደረገ ነው ያለው? ግራ መጋባቴ ጨመረ . . . ከአዲስ አበባ አምኛቸው የመጣሁት እነሱን ነው፡፡ ሐገሩንም ጠንቅቀው ያውቁታል፡፡
የሩቅ ቢሆንም ዝምድና ሳይኖረን አይቀርም፡፡ ሆኖም ጊዜው አስተማማኝ አይደለም፡፡ ምንም የርስ በርሱ ጦርነት ከተጠናቀቀ ሰባት ዓመት
ቢያልፈውም በየመንገዱ የተቃጠለ ታንክ እና የጦር መኪና ማየት ከብርቅ የሚቆጠር አይደለም፡፡ በዛ ላይ ሰዉ ሁሉንም በጥርጣሬ የሚያይ
ስለሚመስል ባይተዋርነትን ያገዝፋል፡፡ ባጠቃላይ ሁኔታው ሁሉ ስጋቴን የሚጨምር እንጂ የሚያቃልል አይደለም፡፡
በዚህ
አይነት ስሜት ውስጥ መቆየት አልፈለኩኝም፤ ጥያቄዬን አጠንክሬ ገፋሁበት፡፡
“ይኽውልህ
የአካባቢው ሰው ማንን እንደሚጠላ እና ከማን ወዳጅነት እንዳለው አይታወቅም፡፡ አንተ ደግሞ ለሐገሩ እንግዳ ነህ፤ አይደለህም አንተ
የትኛውንም ጸጉረ ልውጥን ደግሞ በቀላሉ ማወቅ ይችላሉ”
“እና?”
ለጥያቄዬ በቀጥታ መልስ የሚሰጠኝ አላገኘሁም፡፡
“የአንተን
አባት በቀላሉ ማንም ሰው የሚያውቀው ነው”
“ታዲያ
ይሔ የምትሉኝ ጉዳይ ካባቴ ጋር የሚያገናኘው ምን ነገር አለ፡፡ ደግሞም አባቴ ከሞተ ሃያ ዓመት ሊሆነው ነው፡፡ ምንድን ነው ችግሩ?”
“አባትህ
ጋ አይደለም ችግሩ የሚኖረው፡፡ አባትህ ከዚህ ሀገር ከወጣ ራሱ ሠላሳ ዓመት አልፎታል”
“የምትሉኝ
አልገባኝም በግልጽ ያለውን ችግር ማወቅ ይኖርብኛል” አልኳቸው፡፡
“:ይሔውልኽ!
ችግሩ አያትህ ጋር ነው”
“በግልጽ
ንገሩኝ ምንድን ነው ችግሩ?”
ሁለቱም
እርስ በርሳቸው ተያዩ. . .
ከ ሰባት አመታት በፊት በስራ አጋጣሚ እኔም ብዙ የተዘመረላቸው እና የታሪክ ቓት የሆኑ በስማቸው ገዝፈው የሚጠሩ መንደሮችን የታዘብኩበት እይታዪ ነበር፡፡
ምላሽ ይስጡሰርዝከነኚ ስመ ገናና ከተሞች ስለ አንዱ ብቻ ነቅሼ ላውራ፡ ‹ ወረኢሉ ›፡፡
ከአዝማሪዎቻችን የግጥም ድርደራ ባሻገር የአጤ ሚኒሊክን ወደ አድዋ ሰራዊታቸውን ሲያተሙ ፤ወረኢሉ ከተህ እንዳገኝህ ፤ የሚለው ትዕዛዛችውን ያነበበ ወይ የሰማ
ይህችን ገናና ከተማ እንዴት ይስላት ይሆን? እኔ ያየሁዋት ጊዜ ያቺ በጣም ትንሽ መንደር አንድም ደረጃውን የጠበቀ መንገድ የሌላት፣ በሳምንት ዐንዴ ከሚቆም የገጠር ገበያ ውጪ መደበኛ ግብይት የሌለባት ምስኪን ድህነት የተጫናት የገጠር መንደር ነበረች፡፡
ያንን ባየሁ ጊዜ እኛ ኢትዮጵያውያን እራሳችንን በመካብ ያልሆነውን ስዕል ለራሳችን ሰጥተን (እኛ ልዪ፤ እኛ ቆንጆ፤እኛ ሀገር ወዳድ፤ እኛ ኩሩ ፤እኛ የገናና ታሪክ ባለቤት) ሌላም ሌላም እያልን እስክመቼ እውነተኛ የቆምንበትን እና ያለንበትን ቦታ ካላወቅን ወደፊት መራመድ የማይታሰብ ነው፡፡እኛ በዐለም ፊት የመጨረሻዎቹ
ደሀዎች ነን፤ የማይካድ ሀቅ፤ በድህነት ውስጥ ኩራት፤ ሀገር ወዳድነት፤ገናናነት፤ ተቀባይነት የማይታሰብ ነው፡፡ አዎ መጀመሪያ ድሀዎች ነን እንበል ያለበለዚያ ለራስ የሚሰጥ ትልቅ ግምት ለወረኢሉም ምንም አልጠቀማትም፡፡
ከአንተ ገና ብዙ እንጠብቃለነን፡፡ እንደ ዳንኤል ክብረት በሳል ተወዳጅ እና ተነባቢ ገፅ እንደሚሆን ተስፋአደርጋለሁ፡፡
ምላሽ ይስጡሰርዝkeep the good work.
ምላሽ ይስጡሰርዝ